አሜሪካ መሩ አዲሱ የዲጂታል ቅኝ አገዛዝ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን አጥምዷል - የሳንሱር ባለሙያ

ሰብስክራይብ
አሜሪካ መሩ አዲሱ የዲጂታል ቅኝ አገዛዝ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን አጥምዷል - የሳንሱር ባለሙያ

ቀደምት የቅኝ ግዛት ዘመን "ወርቅና ብርን በመዝረፍና ሀገራትን በማፈራረስ" የሚገለጽ ሲሆን የዲጂታል ዘመኑ አዲስ ቅኝ አገዛዝ ግን "ዜጎችና ሀገራት የተወሰኑ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙ በማስገደድ የግል መረጃዎቻቸውን መዝረፍ" እንደሆነ የቀድሞ የፌስቡክ አጋላጭና የሳንሱር ባለሙያው ራያን ሃርትዊግ ለስፑትኒክ ገልጸዋል።

ከቃለ ምልልሱ የተወሰዱ ሌሎች ዋና ዋና ነጥቦች፦

በደቡባዊው የዓለም ክፍል ሀገራት የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መረጃ ተሰብስቦ ለትርፍ የሚሸጥ በመሆኑ ኢንተርኔት ለዲጂታል ንግድ እንደ መሣሪያነት እያገለገለ ይገኛል።

አሜሪካ "የኢንተርኔት ስሞችና ቁጥሮች ኮርፖሬሽን" በተሰኘው ተቋም አማካኝነት ኢንተርኔትን በበላይነት ትመራለች።

ዓለም አቀፉን መረብ በበላይነት የሚቆጣጠሩት ግዝፎቹ የምዕራብ ኩባንያዎች የግል መረጃ ጥበቃ ደንቦችን ችላ ብለው "መረጃ ይሰበስባሉ።"

እንደ አማዞን፣ ፌስቡክ እና ጎግል ያሉ ግዙፍ ኮርፖሬሽኖች፤ ሀገራት ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን መረጃዎች ሳንሱር እንዲያደርጉ "ተጽዕኖ የመፍጠር" አቅም አላቸው።

የምዕራባውያን ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በደቡባዊው የዓለም ክፍል ሀገራት የዲጂታል መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ፤ የፖሊሲ ውሳኔ እና የኢኮኖሚ ዕድገታቸውን የመቆጣጠር አቅም አግኝተዋል።


"አሜሪካ እንደ ፌስቡክ እና ጎግል ባሉ ወኪሎቿ አማካኝነት፤ መረጃቸውን በመቆጣጠር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ነጻነት ገፋ፤ ዓለም አቀፍ አምባገነንነትን አንግሳለች።"

*ሜታ እና አገልግሎቶቹ በሩሲያ በጽንፈኝነት የታገዱ ናቸው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0