ኢትዮጵያ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የሚያስችል የዲጂታል ሥርዓት ይፋ አደረገች
14:07 24.04.2026 (የተሻሻለ: 14:14 24.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የሚያስችል የዲጂታል ሥርዓት ይፋ አደረገች
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የለማውን የአካባቢ ብክለት ማሳወቂያ ዲጂታል ሥርዓት በይፋ አስመርቋል።
ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ ዜጎች በአካባቢያቸው የሚታዩ የብክለት አደጋዎችን በሞባይል መተግበሪያ እና ድረ-ገጽ አማካኝነት በቀላሉ ለሚመለከተው አካል እንዲጠቁሙ ያስችላል ተብሏል።
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለሊሴ ነሜ፤ “መተግበሪያው በተለይ በከተሞች የተገነቡ የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ እና የጽዳት ሥራዎችን በዘላቂነት ለመጠበቅ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በዲጂታል ስርዓቱ አራት ዋና ዋና ጥቆማዎችን ማቅረብ ይቻላል፦
የአካባቢ ብክለት፣
የኬሚካል እና አደገኛ ቆሻሻ፣
የማዘጋጃ ቤት ቆሻሻ፣
የአካባቢ ሕግ ተከባሪነት ክትትል እና ቁጥጥር ጥቆማ፡፡
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና፤ "ኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ላይ የላቀ ብቃት ለማምጣት ሰው ሠራሽ አስተውህሎትን እንደ ወሳኝ ግብዓት እየተጠቀመች ነው" ብለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X