በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ በከሸፈ ጥቃት 25 አሸባሪዎች ተገደሉ
ከቦኮ ሃራም አንጃ ኢስዋፕ* (የምዕራብ አፍሪካ ክፍለ ግዛት እስላማዊ መንግሥት) ጋር ግንኙነት ያላቸው አሸባሪዎች በቦርኖ ግዛት ኩካሬታ ላይ የሰነዘሩት ጥቃት በናይጄሪያ ጦር መክሸፉ ተገልጿል።
የሀገሪቱ ወታደራዊ ምንጮች እንደገለጹት፦
አቡ ዑመር ቡንዲ ሙንዚር የተባለ ከፍተኛ አዛዥን ጨምሮ 25 አሸባሪዎች ተገድለዋል።
አንድ አሸባሪ በቁጥጥር ስር ሲውል፤ ሁለት ወታደሮች ላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሷል።
18 ኤ.ኬ-47 ጠመንጃዎች፣ መትረየሶች፣ የፀረ-አውሮፕላን መሣሪያዎች፣ ሞርታሮች እና ጥይቶች ተማርከዋል።
ቦኮ ሃራም እና የኢስዋፕ አማፅያን ላለፉት አስርት ዓመታት በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ በፈፀሙት ጥቃት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ በሚሊዮኖች የሚሆኑ ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።
*በሩሲያ እና ሌሎች ሀገራት በአሸባሪነት የተፈረጀ ደርጅት
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X