በኪየቭ ትዕዛዝ በሩሲያ የሚዲያ ተቆጣጣሪ ሮስኮምናዶር ላይ ታቅዶ የነበረ የሽብር ጥቃት መክሸፉን የሩሲያ የደህንነት መሥሪያ ቤት አስታወቀ

የሩሲያ የደህንነት መሥሪያ ቤት
የሩሲያ የደህንነት መሥሪያ ቤት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.04.2026
ሰብስክራይብ
በኪየቭ ትዕዛዝ በሩሲያ የሚዲያ ተቆጣጣሪ ሮስኮምናዶር ላይ ታቅዶ የነበረ የሽብር ጥቃት መክሸፉን የሩሲያ የደህንነት መሥሪያ ቤት አስታወቀ

እስካሁን የታወቁ ዝርዝር መረጃዎች፦

የሽብር ጥቃቱን በማቀናጀት የተሳተፉ ሰባት ጽንፈኛ ቀኝ ዘመም እና የኒዮ-ፋሺስት አስተሳሰብ አራማጅ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የጥቃት ዕቅዱ ፈንጂ በመጠቀም ተሽከርካሪን ማፈንዳት ነበር።

ግለሰቦቹ በዩክሬን የደህንነት መሥሪያ ቤቶች በቴሌግራም አማካኝነት የተመለመሉ ናቸው።

የቡድኑ መሪ የሆነው የሞስኮ ነዋሪ እምቢተኝነቱን በመሣሪያ በማሳየቱ በፀጥታ ኃይሎች ተመትቷል።

1 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፈንጂ፣ ቦምብ፣ ሽጉጦች እና ከዩክሬን ታጣቂዎች ጋር የሚያያዙ ምልክቶች ከተያዙት ቁሳቁሶች መካከልይገኙበታል።

የዩክሬን የደህንነት መሥሪያ ቤቶች የቴሌግራም መተግበሪያን የማገድ እርምጃን ጨምሮ የሩሲያን የመረጃ ደህንነት ለመጠበቅ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማደናቀፍ እየሞከሩ ነው።

ጠላት የጥፋት እና የሽብር ድርጊቶችን፣ ጽንፈኛ እንቅስቃሴዎችን፣ የሳይበር ማጭበርበርን እና ሌሎች ከባድ ወንጀሎችን ለመፈጸም ቴሌግራምን በስፋት እየተጠቀመበት ይገኛል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0