ሩሲያ እና አፍሪካ ተላላፊ በሽታዎችን በጋራ በመዋጋት የሚያደርጉት ትብብር 'ሁለቱንም ተጠቃሚ የሚያደርግ' ነው - የቡርኪና ፋሶ ተመራማሪ

ሰብስክራይብ

ሩሲያ እና አፍሪካ ተላላፊ በሽታዎችን በጋራ በመዋጋት የሚያደርጉት ትብብር 'ሁለቱንም ተጠቃሚ የሚያደርግ' ነው - የቡርኪና ፋሶ ተመራማሪ

ቡርኪና ፋሶ አቅሟን ለማጠናከር ከሩሲያ ተንቀሳቃሽ የላቦራቶሪ ድጋፍ ማግኘቷን በብሔራዊ የሕዝብ ጤና ኢንስቲትዩት የማዕከላዊ ሪፈራል ላቦራቶሪ ዳይሬክተር ኢሲዶር ቦንኩንጉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

ተመራማሪው በብራዛቪል እየተካሄደ ካለው ከሩሲያ-አፍሪካ ተላላፊ በሽታዎችን የመከላከል ኮንፈረንስ ጎን ለጎን ሲናገሩ "ሩሲያ በጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ አስተባባሪነት ሥልጠናዎችንም እየሰጠች ነው" ብለዋል።

የዚህ ዓይነቱ ትብብር በሁለቱም ወገኖች ተጠቃሚነት ላይ በተመሠረተ ማዕቀፍ ውስጥ የእውቀት ልውውጥ እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማሳደግ ዓላማው ያደረገ መሆኑን ቦንኩንጉ ጠቁመዋል።

ኮንፈረንሱ የተዘጋጀው "ሮስፖትሬብናድዞር" በተሰኘው የሩሲያ የጤና ጥበቃ አገልግሎት አማካኝነት ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0