ሕንድ በግንቦት ወር የምታስተናግደውን 4ኛውን የሕንድ-አፍሪካ ፎረም ጉባኤ መለያ አርማ፣ መሪ ቃል እና ድረ-ገፅ ይፋ አደረገች
20:15 23.04.2026 (የተሻሻለ: 20:24 23.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሕንድ በግንቦት ወር የምታስተናግደውን 4ኛውን የሕንድ-አፍሪካ ፎረም ጉባኤ መለያ አርማ፣ መሪ ቃል እና ድረ-ገፅ ይፋ አደረገች
4ኛው የሕንድ-አፍሪካ ፎረም ጉባኤ በፈረንጆቹ ግንቦት 31 ቀን በኒው ዴልሂ እንደሚካሄድ የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። የጉባኤው መሪ ቃል "የሕንድ አፍሪካ ስልታዊ አጋርነት ለፈጠራ፣ ለጥንካሬ እና ለአካታች ለውጥ" የሚል ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኤስ. ጃይሻንካር "አጋርነታችን [...] ምስቅልቅል በበዛበት ዓለም ውስጥ የመረጋጋት፣ እርግጠኝነት በሌለበት ወቅት የታማኝነት እንዲሁም በፈታኝ ጊዜያት የሕብረት መልዕክት ይሆናል" ብለዋል።
ሕንድ በአፍሪካ 17 አዳዲስ ኤምባሲዎችን በመክፈት አጠቃላይ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ቁጥሯን 46 እንዳደረሰች ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። አክለውም አፍሪካ ከሕንድ አጎራባች ሀገራት ውጭ ትልቁን የልማት ድጋፍ የምታገኝ አኅጉር መሆኗንም ገልጸዋል።
ከዋናው ጉባኤ በፊት በግንቦት 29 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ እንዲሁም በግንቦት 28 የከፍተኛ ባለሥልጣናት ስብሰባ ይካሄዳል። የመጨረሻው የሕንድ-አፍሪካ ፎረም ጉባኤ የተካሄደው እ.ኤ.አ በጥቅምት 2015 ነበር።
የጉባኤው አርማ፣ መሪ ቃል እና ድረ-ገጽ ይፋ በሆነበት ሁነት ዙሪያ የጋዜጠኛችንን የቪዲዮ ዘገባ ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X