ዚምባብዌ እና ቦትስዋና ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ዘላቂ ልማትን ለማጎልበት የሚያስችሉ 10 የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራረሙ

ሰብስክራይብ

ዚምባብዌ እና ቦትስዋና ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ዘላቂ ልማትን ለማጎልበት የሚያስችሉ 10 የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራረሙ

ስምምነቶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

◻ የልምድ ልውውጥ ሥልጠናዎችን ጨምሮ የመከላከያ መስክ ትብብር፣

◻ ፍትሕ፣ ደህንነት እና የሰዎች ዝውውርን በተመለከተ፤ የታሰሩ ሰዎችን ማስተላለፍ፣ የኢሚግሬሽን ትብብር እንዲሁም በእስር ቤት እና በማረሚያ አገልግሎቶች ዙሪያ መሥራት፣

◻ በሕግ ማስከበር እና የደህንነት ትብብር፤ የከብት ስርቆትን መከላከል፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን መዋጋት እና የሲቪል አውሮፕላን አደጋዎች እና ክስተቶች ምርመራ፣

◻ በኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ልማት ዙሪያ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ማስተዋወቅ እንዲሁም በአፍሪካ የነጻነት ሙዚየም ላይ በጋራ መሥራት።

ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋጓ ስምምነቶቹ ንግድን እንደሚያፋጥኑ፣ ኢንቨስትመንትን እንደሚያሳድጉ፣ የኢንዱስትሪ ትብብርን እንደሚያጠናክሩ እና ዘላቂ ልማትን እንደሚያራምዱ ገልጸው፤ ፈጣን አፈፃፀም እና የሚታዩ ውጤቶች እንዲመዘገቡ አሳስበዋል።

ፕሬዚዳንት ዱማ ጊዲዮን ቦኮ በበኩላቸው፤ አፍሪካውያን የራሳቸውን የልማት ትርክት በባለቤትነት ሊመሩ እንደሚገባ አሳስበዋል። ሚዲያዎችም ከአሉታዊ የውጭ ምስሎች ይልቅ በአኅጉሪቱ ዙሪያ አዎንታዊ ትርክቶችን እንዲያጎሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0