ናይጄሪያ አየር መንገዶችን ከመዘጋት ለመታደግ ዕዳ ለመሰረዝ ወሰነች
17:00 23.04.2026 (የተሻሻለ: 17:04 23.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ አየር መንገዶችን ከመዘጋት ለመታደግ ዕዳ ለመሰረዝ ወሰነች
የሀገሪቱ የአቪዬሽን ሚኒስትር ፌስቱስ ኪያሞ እንደገለጹት፤ ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ከተወያዩ በኋላ የሀገር ውስጥ አየር መንገዶች ለአቪዬሽን ኤጀንሲዎች ያልከፈሉት ዕዳ በከፊል እንዲሰረዝ ተስማምተዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም አየር መንገዶቹ የዕዳ ስረዛ ጥያቄያቸውን ሳይዘገዩ በይፋ እንዲያቀርቡ መመሪያ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል። የሚሰረዘው የዕዳ መጠን በፕሬዚዳንቱ የመጨረሻ ውሳኔ ይታወቃል።
በተጨማሪም መንግሥት የሀገር ውስጥ በረራዎችን በተመለከተ በአየር መንገዶች እና በተጓዦች ላይ የሚደርሰውን ጫና ለማብረድ የሚጣሉ ታክሶች እና ክፍያዎችን በመገምግም የውሳኔ ሃሳብ የሚያቀርብ ኮሚቴ ያዋቅራል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X