በኢትዮጵያ በአካባቢ ተሰማሚ የሆነ የሥነ-ህንጻ ምህዳር እውን ለማድረግ እየተሠራ ነው ተባለ

ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ በአካባቢ ተሰማሚ የሆነ የሥነ-ህንጻ ምህዳር እውን ለማድረግ እየተሠራ ነው ተባለ

ቢግ ፋይቭ ኮንስትራክት ኢትዮጵያ የተሰኘ ዓለም አቀፍ የሥነ-ህንጻ እና የግንባታ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በአውደ ርዕዩ ላይ ኢትዮጵያ፣ ቱርኪዬ፣ ቻይና እና ህንድን ጨምሮ ከ120 ሀገራት የተወጣጡ የሥነ-ህንፃ እና የግንባታ ግብዓቶች አምራቶች ምርት እና አገልግሎታቸውን አያስተዋወቁ ነው ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

መድረኩ ዓለም አቀፍ የግንባታ ግብዓት አምራቾች፣ አከፋፋዮች፣ መሐንዲሶች እና የግንባታ አማካሪዎች ከሀገር ዉስጥ ባለድርሻ ኣካላት ጋር ትስስር የሚፈጥሩበት እንደሚሆን አዘጋጆቹ ገልፀዋል።

የአረንጓዴ ግንባታ ምክር ቤት የተሰኘ የዘርፉ አማካሪ ድርጀት ዋና ዳይሬክተር ሊቀ ሰሎሞን፤ በሀገሪቱ የአረንጓዴ ግንባታ መርሆዎችን በስፋት ተፈፃሚ በማድረግ ለአካባቢ ተሰማሚ የሆነ የሥነ-ህንፃ ምህዳር ለመፍጠር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0