የኢትዮጵያ የግብርና ሜካናይዜሽን አንድ ሦስተኛው የእርሻ መሬት በትራክተር እንዲታረስ ማስቻሉ ተገለፀ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የግብርና ሜካናይዜሽን አንድ ሦስተኛው የእርሻ መሬት በትራክተር እንዲታረስ ማስቻሉ ተገለፀ

በሀገሪቱ 7 ሚሊዮን ሄክታር የእርሻ መሬት በትራክተር በማረስ የግብርናውን ዘርፍ ከልማዳዊ አሠራር ወደ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲሸጋገር እየተደረገ መሆኑን የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ ገልፀዋል።

የትራክተሮች ቁጥር ወደ 27 ሺህ፣ የኮምባይነሮች ከ8 ሺህ በላይ እንዲሁም የውኃ ፓምፖች ከ280 ሺህ በላይ መድረሱንም ጠቅሰዋል።

የግብርና ማሽነሪዎች ከቀረጥ ነፃ መግባታቸው እና ለአርሶ አደሮች የብድር አቅርቦት መመቻቸቱ ለዘርፉ ዕድገት ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል።

ይህ ሂደት ግብርናውን ከሰውና ከእንስሳት ጉልበት እንዲሁም ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ ምርታማነትን ለማሳደግ የተያዘውን ግብ እያሳካ ነው ማለታቸውን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0