አሜሪካ በኳታር የሚገኙ 1,100 አፍጋኒስታውያንን በኮንጎ ለማስፈር ንግግር ላይ መሆኗ ተገለፀ

ሰብስክራይብ

አሜሪካ በኳታር የሚገኙ 1,100 አፍጋኒስታውያንን በኮንጎ ለማስፈር ንግግር ላይ መሆኗ ተገለፀ

የትራምፕ አስተዳደር በኳታር በሚገኝ የቀድሞ የአሜሪካ ወታደራዊ ካምፕ የኢሚግሬሽን ቪዛ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ አፍጋኒስታውያንን ወደ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ለማዛወር ከሀገሪቱ ጋር ድርድር እያደረገ መሆኑን "አፍጋን ኢቫክ" የተሰኘ የቀድሞ ወታደሮች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጥምረት አስታውቋል።

ከሠፋሪዎቹ መካከል በአፍጋኒስታን ጦርነት ወቅት የሠሩ አስተርጓሚዎች፣ የቀድሞ የአፍጋኒስታን ልዩ ኦፕሬሽን ኃይሎች እና የአሜሪካ ጦር አባላት ዘመዶች ተካተዋል።

"አፍጋን ኢቫክ" ዕቅዱ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ካለው ከፍተኛ የጸጥታ ችግር እና ሰብዓዊ ቀውስ አኳያ "ተቀባይነት የሌለው" ነው ሲል ተቃውሞውን ገልጿል።

የትራምፕ አስተዳደር ሥልጣን መያዙን ተከትሎ የአፍጋኒስታውያን የቪዛ ሂደት በመቋረጡ ብዙዎቹ በእልባት እጦት ቆይተዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ግለሰቦቹ በሦስተኛ ሀገር በመቋቋማቸው አዲስ የህይወት ዕድል እንደሚያገኙ ሲገልጽ፤ ኮንጎ እስካሁን በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠችው አስተያየት የለም።

የማህደር ቪዲዮው እ.ኤ.አ በነሐሴ 2021 ታሊባን አፍጋኒስታንን ከተቆጣጠረ በኋላ አሜሪካ ከካቡል ስትወጣ የነበረውን ትርምስ ያሳያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0