ሩሲያዊ የሥነ-ምድር ተመራማሪ በሰንሰለት እስር፣ በከፍተኛ ሙቀት ለግማሽ ዓመት ታግቶ በቆየባት አፍሪካ የመመለስ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

ሰብስክራይብ

ሩሲያዊ የሥነ-ምድር ተመራማሪ በሰንሰለት እስር፣ በከፍተኛ ሙቀት ለግማሽ ዓመት ታግቶ በቆየባት አፍሪካ የመመለስ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

በቅርቡ ከማሊ ታጠቂዎች እገታ ነፃ የወጣው ዩሪ ዩሮቭ፤ እሱና የሥራ ባልደረባው ለስድስት ወራት ያህል ሌሊቱን በሰንሰለት እስርና ረሃብ እንዲሁም ያለ መጠለያ ለአምስት ወራት 50 ዲግሪ ሴልሺየስ በሚደርስ ሙቀት ውስጥ እንዳሳለፉ ለጋዜጠኞች ተናግሯል።

“አያያዛቸው ይለያያል፤ አንዳንዴ በጥሩ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በመጥፎ ሁኔታ ይይዙን ነበር። በጣም ከባድ ነበር” ሲልም ተናግሯል።

ለአንድ የሩሲያ ኩባንያ የሚሠሩት ሁለቱ ጂኦሎጂስቶች፤ እ.ኤ.አ በ2024 ከአል-ቃይዳ* ጋር ግንኙነት ባለው ቡድን በኒጀር ታግተው ነበር።

ይሁ ሁሉ መከራ የደርሰበት ዩሮቭ፤ እስካሁን ከባለቤቱ ጋር ባይወያይም አሁንም ወደ አፍሪካ ተመልሶ መሥራት እንደሚፈልግ ገልጿል።

እሱና የሥራ ባልደረባው ኦሌግ ግሬታ በማሊ ውስጥ በሚገኘው የሩሲያ “አፍሪካ ኮርፕ” ነፃ ከወጡ በኋላ ለሕክምና ወደ ሞስኮ ተልከዋል።

*በሩሲያ እና በሌሎች በርካታ ሀገራት የታገደ የሽብር ድርጅት

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0