ኢትዮጵያ እና ኬንያ ቀጣናዊ እና የዲጂታል ግንኙነታቸውን ለማፋጠን ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ኬንያ
ኢትዮጵያ እና ኬንያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.04.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ኬንያ ቀጣናዊ እና የዲጂታል ግንኙነታቸውን ለማፋጠን ተስማሙ

ሁለቱ ጎረቤት ሀገራት አዲስ አበባ ውስጥ ባካሄዱት ውይይት "የአፍሪካ ቀንድ መግብያ በር ልማት ፕሮጀክት" አፈጻጸምን ለማፋጠን ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።

በፕሮጀክቱ የተካተቱ ግቦች፦

ወደ 1,000 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የፋይበር ኦፕቲክ መሠረተ ልማት በመዘርጋት ቀልጣፋና አስተማማኝ የዲጂታል መተላለፊያ መገንባት፣

የጉምሩክ ትብብርን ማጠናከር፣

በማልካ ሱፍቱ እና በማልካ ላዴኒ በኩል የሚያገናኙ ድልድዮችን መገንባትና የጋራ የድንበር ኬላዎችን ማቋቋም።

ፕሮጀክቱ የድንበር ተሻጋሪ ንግድን ለማቀላጠፍ፣ የጉምሩክ ትብብርን ለማሳደግና ኬንያን ከኢትዮጵያና ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጋር በዲጂታል በማስተሳሰር የቀጣናው የንግድ ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0