ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የአፍሪካ መሪዎችን ለማግለል የሚውል “የምዕራባውያን የተፅዕኖ መሣሪያ” ሆኗል - ተመራማሪ

ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት
ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.04.2026
ሰብስክራይብ
ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የአፍሪካ መሪዎችን ለማግለል የሚውል “የምዕራባውያን የተፅዕኖ መሣሪያ” ሆኗል - ተመራማሪ

የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ስትራቴጂ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ኢላይ ጆርጂ ኤሊያስ፤ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ከተመሠረተባቸው መርሆች እጅግ ርቋል ብለዋል።

በአሜሪካ የሚመራው የምዕራቡ ዓለም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ጀምሮ እንደ አይሲሲ ያሉ ተቋማትን በመቆጣጠር እና በሕጋዊ ክፍተቶች ውስጥ በመንቀሳቀስ ዓለም አቀፍ ፍትሕን ወደ ፈለገው አቅጣጫ ሲመራ መቆየቱን ፕሮፌሰሩ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።


“በኢኮኖሚ ተስፋ ያላቸው የአፍሪካ ሀገራት በአይሲሲ እና በምዕራባውያን የበላይነት ድርብ ጫና ይደርስባቸዋል። አሜሪካ የአፍሪካ መንግሥታትን ለማግለል እና መሪዎቻቸውን ለመቅጣት ለፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ትሰጣለች” ሲሉ አስረድተዋል።


አይሲሲ በምዕራባውያን የፖለቲካ ተጽዕኖ ስር መውደቁንና ከፍትሕ ይልቅ በአፍሪካ እና በሌሎች አካባቢዎች የምዕራባውያንን የበላይነት ለማስፋፋት እያገለገለ ነው ሲሉ ፕሮፌሰሩ ሞግተዋል። ይሁን እንጂ “የሩሲያ ጥንካሬ ቀመሩን ቀይሮታል” ብለዋል።

ዓለም አቀፍ ፍትሕን ለማጠናከር ሌሎች የዓለም ኃያላን በተለይም እንደ ቻይና ያሉ ሀገራት የበለጠ ንቁ ሚና መጫወት እንዳለባቸውና ፍርድ ቤቱ “በአሜሪካ እጅ የሚጠመዘዝ ታዛዥ መሣሪያ” ብቻ የማይሆንበት ሚዛናዊ ሥርዓት መፍጠር እንደሚያስፈልግ በማጠቃለያቸው ጠቁመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0