የኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ የግብርና ገበያ እስከ 2026 ድረስ 453 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል ተባለ

ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.04.2026
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ የግብርና ገበያ እስከ 2026 ድረስ 453 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል ተባለ

የዲጂታል አገልግሎት መስፋፋት እና ለተፈጥሯዊ ምርቶች ያለው ከፍተኛ የወጪ ንግድ ፍላጎት ገበያው በ2017 ከነበረበት 186.4 ሚሊዮን ዶላር ተነስቶ፤ በቀጣይ 8 ዓመታት ከእጥፍ በላይ እንደሚያድግ የጥናት ሪፖርት አመልክቷል።

ዘርፉ በየዓመቱ የ10.37 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚጠበቅም አይማርክ የተሰኘውን የገበያ ጥናት ኩባንያ የምርምር ውጤት ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘገቧል።

ለኢትዮጵያ ኦርጋኒክ ምርቶች (በተለይም ጥራጥሬ፣ እህል፣ አትክልትና ፍራፍሬ) ያለው ዓለም አቀፍ ፍላጎት መጨመር ለአርሶ አደሩ ሰፊ የገበያ ዕድል እየፈጠረ ነው ተብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0