የሩሲያ የቫልዳይ የውይይት ክለብ በፖለቲካ እና ምጣኔ ሃብት ዘርፎች ለወጣት ተመራማሪዎች የፕሮግራም ማመልከቻዎችን ክፍት አደረገ

ሩሲያ
ሩሲያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.04.2026
ሰብስክራይብ
የሩሲያ የቫልዳይ የውይይት ክለብ በፖለቲካ እና ምጣኔ ሃብት ዘርፎች ለወጣት ተመራማሪዎች የፕሮግራም ማመልከቻዎችን ክፍት አደረገ

የ "ቫልዳይ - አዲስ ትውልድ" ፕሮግራም ተሳታፊዎች፦

◻ በክለቡ ድረ-ገጽ ጥናቶችን ማሳተም፣
◻ በዝግጅቶቹ ላይ መሳተፍ፣
◻ የቫልዳይ ባለሙያነት ደረጃን ማግኝት ይችላሉ።

ማመልከቻው እስከ ግንቦት 24፣ 2018 ዓ.ም ድረስ ክፍት ይሆናል።

በመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም የመጀመሪያው የወጣቶች ኮንፈረንስ "2040ን መቅረጽ፦ እየተገነባ ባለው ዓለም ውስጥ የወጣቱ ትውልድ ግንዛቤ" በሚል መሪ ቃል ከተካሄደ በኋላ፤ ፕሮጀክቱ ከ70 በላይ ጥናቶችን ያሳተመ ሲሆን 30 የዝግ የባለሙያ ስብሰባዎችን አስተናግዷል። በአሁኑ ወቅት ከ15 ሀገራት የተውጣጡ ከ23 እስከ 35 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ተመራማሪዎችን ያሰባስባል።

ተሳታፊዎች በቀጣይ ዓመት በባለሙያዎች ድጋፍ የትንታኔ ጽሁፎችን በማዘጋጀት እንዲሁም በውይይቶች እና ኮንፈረንሶች ላይ የሚካፈሉ ይሆናል፡፡ በመጨረሻው ኮንፈረንስም በቁልፍ ዓለም አቀፋዊ እና ክልላዊ አዝማሚያዎች ላይ የጋራ ሪፖርት እንደሚቀርብ የክለቡ የፕሬስ አገልግሎት ገልጿል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0