በናይጄሪያ ስድስት ግለሰቦች በሀገር ክህደት ወንጀል ተከሰሱ

በናይጄሪያ ስድስት ግለሰቦች በሀገር ክህደት ወንጀል ተከሰሱ
በናይጄሪያ ስድስት ግለሰቦች በሀገር ክህደት ወንጀል ተከሰሱ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.04.2026
ሰብስክራይብ
በናይጄሪያ ስድስት ግለሰቦች በሀገር ክህደት ወንጀል ተከሰሱ

የናይጄሪያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ፣ እ.ኤ.አ. በ2025 ከከሸፈው የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ እና ስልጣን የመያዝ እቅድ ጋር በተያያዘ ስድስት ግለሰቦችን በሀገር ክህደት ወንጀል መክሰሳቸውን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

አቃቤ ሕግ በፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ ላይ የመንግስት ግልበጣ ለማድረግ አቅደዋል በሚል በተጠረጠሩት ግለሰቦች ላይ 13 ክሶችን ያካተተ የክስ መዝገብ አቅርቧል። ክሱ በአቡጃ ለሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቅረቡን ዘገባው አመልክቷል።

በመንግሥት ግልበጣ ሙከራው ውስጥ ተሳትፈዋል ተብለው ከተከሰሱት መካከል የቀድሞው የባየልሳ ግዛት አስተዳዳሪ ቲሚፕሬ ሲልቫ፣ ሜጀር ጀነራል መሐመድ ኢብራሂም ጋና፣ ካፒቴን ኢራስመስ ኦቼጎቢያ ቪክቶር እና ኢንስፔክተር አህመድ ኢብራሂም ይገኙበታል።

የፍርድ ሂደቱ ረቡዕ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

በጥቅምት ወር 2025 16 የናይጄሪያ ጦር መኮንኖች በቁጥጥር ስር ውለው የነበረ ሲሆን፣ ቆይቶ እንደታወቀው ወታደራዊ ኃላፊዎቹ የታሰሩት የመንግስት ግልበጣ በማዘጋጀት ተጠርጥረው እንደነበር ይታወሳል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0