ታንዛኒያ የመጀመሪያውን የ'ሚስ ወርልድ ታንዛኒያ' ውድድር አካሄደች
18:47 21.04.2026 (የተሻሻለ: 18:54 21.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ታንዛኒያ የመጀመሪያውን የ'ሚስ ወርልድ ታንዛኒያ' ውድድር አካሄደች
ከዳሬ ሰላም የመጣችው የ24 ዓመቷ ላቲሪሺያ ኢያን የመጀመሪያዋ "ሚስ ወርልድ ታንዛኒያ" በመሆን ዘውድ መድፋቷን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ኢያን እ.ኤ.አ. በ2026 ከነሐሴ እስከ መስከረም በቬትናም በሚካሄደው 75ኛው የዓለም የቁንጅና ውድድር ላይ ሀገሯን ወክላ ትሳተፋለች።
በተጨማሪም፣ አሸናፊዋ የ38 ሺህ ዶላር ሽልማት ማግኘቷን መገናኛ ብዙኃኑ ጠቅሰዋል።
ሁለተኛ ደረጃን ዳሬ ሰላምን የወከለችው ኖሩ ማሱድ ስትይዝ፤ ሦስተኛ ደረጃ ደግሞ ከሀገሪቱ ማዕከላዊ አስተዳደር ዞን የመጣችው ፓውሊና አሉቴ አግኝታለች።
የ2025 የሚስ ወርልድ አሸናፊዎቹ፣ ኢትዮጵያዊቷ ሚስ ወርልድ አፍሪካ ሐሴት ደረጄ እና ታይላንዳዊቷ ኦፓል ሱቻታ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ታድመዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X