ኢትዮጵያ የታሪክ አጠባበቅ ከባህላዊ የሰነድ አያያዝ ወደ "ነቃ የዲጂታል ሥነ-ምኅዳር" የሚያሸጋግር ስትራቴጂ ይፋ አደረገች
18:16 21.04.2026 (የተሻሻለ: 18:25 21.04.2026)
© Sputnik
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የታሪክ አጠባበቅ ከባህላዊ የሰነድ አያያዝ ወደ "ነቃ የዲጂታል ሥነ-ምኅዳር" የሚያሸጋግር ስትራቴጂ ይፋ አደረገች
ስትራቴጂው ይፋ የሆነው የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን “የኢትዮጵያ ቅርስ ምርምር በዲጂታል ዘመን” በሚል መሪ ቃል እያካሄደ ባለው 3ኛው ዓመታዊ የቅርስ ጥናት ጉባኤ ላይ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው፣ ስትራቴጂው ቅርሶችን እና ታሪካዊ ቦታዎችን በትክክለኛ ሁኔታ መመዝገብ የሚያስችል እንደ ሌዘር ስካኒንግ እና ፎቶግራም ሜትሪ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን ጥቅም ላይ ማዋልን እንደሚያካትት ተናግረዋል ስትል የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግባለች ፡፡
በጉባኤው በቅርስ እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት፣ በቅርስ ምዝገባና ዲጅታል ትራንስፎርሜሽን፣ የአርኪኦሎጂና የፓሌኦንቶሎጂ ቅርሶች፣ የቅርስ ጥበቃና ዘላቂ ልማት እና የቅርስ አስተዳደርና ፖሊሲ ጨምሮ 13 አዳዲስ የምርምር ጽሑፎች እንደሚቀርቡ ተመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ያስተዋወቀው አዲሱ ስትራቴጂ ያካተታቸውን ይዘቶች ለማወቅ የቪዲዮ ጥንቅር ይመለከቱ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X