ኡጋንዳ የውጭ ምንዛሬ ክምችቷን ለማስፋት የሀገር ውስጥ የወርቅ ግዢ ጀመረች – ማዕከላዊ ባንክ
15:42 21.04.2026 (የተሻሻለ: 15:44 21.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኡጋንዳ የውጭ ምንዛሬ ክምችቷን ለማስፋት የሀገር ውስጥ የወርቅ ግዢ ጀመረች – ማዕከላዊ ባንክ
የኡጋንዳ ባንክ ለሦስት ዓመታት በሚቆይ የሙከራ መርሃ ግብር የወርቅ ግዢ እንደምትፈጽም ይጠበቃል፡፡ ይህም ክምችቷን በማስፋት ረገድ ኬንያን እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን እንድትቀላቀል ያደርጋታል።
ኡጋንዳ ባንኩ እንዳስታወቀው መርሃ ግብሩ የሚከተሉትን አልሟል፦
▪በሀገር ውስጥ የሚመረተውን ወርቅ በማካተት የውጭ ምንዛሬ ክምችትን ማስፋት፣
▪አስተማማኝ ክምችትን ማጎልበት እና በባህላዊ መሣሪያዎች (የገንዘብ ሰነዶች) ጥገኝነት መቀነስ፣
▪የሀገር ውስጥ እሴት በመጨመርን ማበረታት እና ጠንካራ የኢኮኖሚ ትስስር በመፍጠር የወርቅ ዘርፉን ወደ መደበኛ ሥርዓት ማስገባት እና
▪የወርቅ ምንጭን የመከታተያ ዘዴዎችን ማሻሻል።
ኡጋንዳ በአሁኑ ወቅት የወርቅ ማዕከል ሆናለች፤ ባለፈው ዓመት የ5.8 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የወርቅ ኤክስፖርት ያስመዘገበች ሲሆን፣ ይህም ከ2024 ጋር ሲነጻጸር የ76% ጭማሪ አሳይቷል። ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን የሀገሪቱ ውስጥ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ በአነስተኛ አምራቾች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X