የኢትዮጵያ የድኅረ ክፍያ ዲጂታል ገበያ ዘርፍ ዋጋ እስከ 2026 58.84 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል ተባለ
14:05 21.04.2026 (የተሻሻለ: 14:14 21.04.2026)
© Sputnik
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የድኅረ ክፍያ ዲጂታል ገበያ ዘርፍ ዋጋ እስከ 2026 58.84 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል ተባለ
አይ.ኤም.ኤ.አር.ሲ ግሩፕ ይፋ ባደረገው አዲስ የጥናት ሪፖርት መሠረት፣ በኢትዮጵያ “አሁኑኑ ይግዙ፣ በኋላ ይክፈሉ” የዲጂታል ብድር ገበያ እ.ኤ.አ በ2025 11.58 ሚሊዮን ዶላር ከነበረበት የዘርፉ ዋጋ፣ በየዓመቱ የ19.8 በመቶ ዕድገት ያሳያል ተብሏል።
የዲጂታል መሠረተ ልማት እና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚው ማኅበረሰብ በከተማዋ በመከማቸቱ፣ አዲስ አበባ የገበያውን 41.6 በመቶ ድርሻ መያዟ ተገልጿል።
ከኦንላይን ግብይት መስፋፋት ጋር ተያይዞ 58.7 በመቶ የሚሆነው የብድር አገልግሎት የሚከናወነው በኢንተርኔት አማካኝነት መሆኑም ተመልክቷል።
የቴሌብር እና ኤም-ፔሳ ተጠቃሚዎች ቁጥር መጨመር፣ የብሔራዊ ባንክ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ እና የኢ-ኮሜርስ ግብይት በየዓመቱ በ25.7 በመቶ ማደጉ ለዘርፉ መስፋፋት እንደ ዋነኛ ምክንያት ተጠቅሰዋል።
ይህ አዲስ አሠራር ሸማቾች ውድ የሆኑ ዕቃዎችን አሁኑኑ ገዝተው ክፍያውን በየወሩ በክፍፍል እንዲከፍሉ በማስቻል የገበያ አቅምን ያሳድጋል ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X