ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የኤሌክትሮቴክኒካል ኮሚሽን በታዳሽ ኃይልና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ለመተባበር ተስማሙ

ኢትዮጵያና ዓለም አቀፉ የኤሌክትሮቴክኒካል ኮሚሽን
ኢትዮጵያና ዓለም አቀፉ የኤሌክትሮቴክኒካል ኮሚሽን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.04.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያና ዓለም አቀፉ የኤሌክትሮቴክኒካል ኮሚሽን በታዳሽ ኃይልና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ለመተባበር ተስማሙ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ እንዳለው መኮንን ከዓለም አቀፉ የኤሌክትሮቴክኒካል ኮሚሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፊሊፔ ሜትዛገር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ የሚመረቱ የሶላር ፓነሎች፣ ትራንስፎርመሮች እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁና በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ኮሚሽኑ የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ሀገሪቱ በዘርፉ እያከናወነች ያለችውን ሰፊ ሥራ ከግምት በማስገባት፣ በኮሚሽኑ ውስጥ ያላት የተባባሪ አባልነት ደረጃ ወደ ሙሉ አባልነት እንዲያድግ ሚኒስቴሩ ጥያቄ አቅርቧል።

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ የኮሚሽኑን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ፍላጎት እንዳላት በይፋ ገልጻለች።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0