የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ለኢብራሂም ትራኦሬ ለሀገራዊ ሰላምና መረጋጋት ላሳዩት ጽኑ ቁርጠኝነት የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ

ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ለኢብራሂም ትራኦሬ ለሀገራዊ ሰላምና መረጋጋት ላሳዩት ጽኑ ቁርጠኝነት የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ

የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኤቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ በኡጋዱጉ ባደረጉት የሥራ ጉብኝት ከቡርኪና ፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ ጋር መገናኘታቸውን የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

▪ ኤቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ከውይይቱ በኋላ፣ ስለ "ሳሕል ቀጣና እና ስለ ቡርኪና ፋሶ ህዝብ ተጨባጭ እውነታ" የተሻለ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

▪ በተጨማሪም "ወደ የጋራ መጻኢ እድል አብሮ ለመጓዝ" የሚያስችል "ትክክለኛ እና ተጨባጭ ሪፖርት" ለአፍሪካ ሕብረት ለማዘጋጀት ማቀዳቸውን ገልጸዋል።

በንዳይሺሚዬ እና በትራኦሬ መካከል የተደረገው ውይይት በአሁኑ ወቅት ከአባልነታቸው የታገዱት የሳሕል አባል ሀገራት እና በአፍሪካ ሕብረት መካከል "የትብብር ድልድይ ለመገንባትና ለማጠናከር በሚያስችሉ መንገዶች" ላይ ያተኮረ እንደነበር የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ይፋ አድርጓል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0