በሜክሲኮ ፒራሚድ አካባቢ በተፈጸመ ተኩስ አንድ ቱሪስት ሲገደል ሌሎች በርካቶች ቆሰሉ
11:47 21.04.2026 (የተሻሻለ: 11:54 21.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በሜክሲኮ ፒራሚድ አካባቢ በተፈጸመ ተኩስ አንድ ቱሪስት ሲገደል ሌሎች በርካቶች ቆሰሉ
▪ ተኩሱ የተካሄደው ከሜክሲኮ ሲቲ አቅራቢያ በሚገኘው የቴኦቲዋካን ጥንታዊ የታሪክ ቦታ ውስጥ በሚገኘውና "የጨረቃ ፒራሚድ" ተብሎ በሚጠራው ታዋቂ የመታሰቢያ ሐውልት አካባቢ እኩለ ቀን ላይ ነው።
▪ እንደ ባለሥልጣናቱ ገለጻ ከሆነ፣ አንድ የታጠቀ ግለሰብ በህንጻው አጋማሽ ላይ ከሚገኝ መድረክ ላይ ሆኖ ተኩስ ከከፈተ በኋላ ራሱን ገድሏል።
▪ በሜክሲኮ ግዛት የደህንነት ሚኒስትር መረጃ መሠረት፣ አንድ ካናዳዊ ቱሪስት ሲገደል፤ ሌላ አንድ ካናዳዊ፣ ሁለት ኮሎምቢያውያን እና አንድ ሩሲያዊ በድምሩ አራት ሰዎች ቆስለው ሕክምና ለማግኘት ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።
▪ የቴኦቲዋካን ፒራሚዶች በሜክሲኮ ቀዳሚ ከሚባሉ የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን፤ ባለፈው ዓመት ብቻ ወደ 722 ሺ የሚጠጉ ጎብኚዎችን አስተናግደዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X