አፍሪካ የኢነርጂ ቀውሱን እንደ መልካም አጋጣሚ ልትጠቀምበት ትችላለች - ባለሙያ

ሰብስክራይብ

አፍሪካ የኢነርጂ ቀውሱን እንደ መልካም አጋጣሚ ልትጠቀምበት ትችላለች - ባለሙያ

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ግጭት፣ በሆርሙዝ ባሕረ ሰላጤ ላይ ለሚታየው መስተጓጎል አፍሪካን እንደ አስተማማኝ የነዳጅ አቅራቢ በመፈረጅ ስልታዊ ጠቀሜታዋን ከፍ አድርጎታል ሲሉ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ የውህደት ፈተናዎች ባለሙያ የሆኑት ኦሴ ሳፊ ቦአሄማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።

አፍሪካ አሁን ያለውን የነዳጅ ቀውስ በዲሲፕሊን የታጀቡ ፖሊሲዎችን በመተግበር "ዘላቂ ልማት እና እውነተኛ የኢነርጂ ሉዓላዊነት" ለማረጋገጥ ልትጠቀምበት ይገባል ሲሉ አክለዋል።

እንደ ቦአሄማ ገለጻ፣ ናይጄሪያ ከአፍሪካ የኢነርጂ ግዙፍ ሀገራት አንዷ እንደመሆኗ መጠን ለጎረቤት ሀገራት ነዳጅ ማቅረብ ትችላለች፤ ነገር ግን የምዕራብ አፍሪካ መንግስታት በራሳቸው ውል ለመገበያየት እና ቀጣናዊ ውህደትን ለማጠናከር የራሳቸውን የክፍያ ስርዓት መዘርጋት ይኖርባቸዋል።

ይሁን እንጂ ናይጄሪያ ስልታዊ የድፍድፍ ነዳጅ ክምችት እና እንደ የባሕር በታች መሐንዲሶች ያሉ ልዩ ባለሙያዎች እጥረት እንዳለባት ባለሙያዋ አሳስበዋል። የሀገሪቱ የነዳጅ ማጣሪያ ሞዴል ሙሉ በሙሉ ዘላቂ ሊሆን የሚችለው መንግሥት በሚከተሉት ላይ ኢንቨስት ካደረገ ብቻ ነው፦

🟠ስትራቴጂያዊ ክምችቶችን መገንባት፣ 

🟠የቧንቧ መስመሮችን ደህንነት መጠበቅና 

🟠የሰው ኃይል ሥልጠናን ማፋጠን።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0