በአሁኑ ወቅት 9.2% የደረሰው የኢኮኖሚ ዕድገት ወደ 10.2 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል - የኢትዮጵያ መንግሥት ሪፖርት

ሰብስክራይብ
በአሁኑ ወቅት 9.2% የደረሰው የኢኮኖሚ ዕድገት ወደ 10.2 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል - የኢትዮጵያ መንግሥት ሪፖርት

ባለፉት ስምንት ዓመታትም በአማካይ 7.5 በመቶ ዕድገት ሲመዘገብ መቆየቱን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው የ100 ቀናት ግምገማ እና የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አስታውቋል።

በሪፖርቱ የተካተቱ ዋና ዋና ቁጥራዊ መረጃዎች

▪ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከ8 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ወጥተው ባለፉት ዘጠኝ ወራት 2.1 ትሪሊዮን ብር ገቢ አመዝግበዋል፡፡

▪ የኢንቨስትመንት ከባቢው በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻሉን ተከትሎ 2,153 የኢንቨስትመንት ፈቃዶች ተሰጥተዋል፡፡

▪በዘጠኝ ወራት ውስጥ ወደ 96 ሺህ የሚጠጉ የሥራ ዕድሎች ተፈጥሯል፡፡

▪ የግብርና ሜካናይዜሽን ማደግ፣ የማምረቻ ዘርፍ የገበያ ድርሻ ከ25 ወደ 46 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡

በሌላ በኩል የብሪክስ አባልነት፣ በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮሩ አጋርነቶች መስፋፋት፣ የኮፕ 32 ጉባኤን ለማስተናገድ መመረጥ እንዲሁም የባሕር በር ለማግኘት የሚደረገው ጥረት ተጠቃሽ የንቁ ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች መሆናቸው በሪፖርቱ ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0