የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን የአፍሪካ ፓትርያርክ ሴኔጋል ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥርዓተ ቅዳሴ አከናወኑ
18:15 20.04.2026 (የተሻሻለ: 18:24 20.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን የአፍሪካ ፓትርያርክ ሴኔጋል ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥርዓተ ቅዳሴ አከናወኑ
የካይሮ እና የሰሜን አፍሪካ ሜትሮፖሊታን እንዲሁም የአፍሪካ ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ቆስጠንጢኖስ፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሚስዮናዊ በሆኑት በቀሲስ ጊዮርጊ ማክሲሞቭ ታጅበው ዳካር ገብተዋል።
በሴኔጋል እና በጋምቢያ የሩሲያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዲሚትሪ ኩራኮቭ፣ የዲፕሎማቲክ አባላት እና በሀገሪቱ የሚኖሩ የሩሲያ ተወላጆች በሥርዓተ ቅዳሴው ላይ ተገኝተዋል።
ከቅዳሴው በኋላ ብፁዕነታቸው ምዕመናንን ለበዓሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ የአባትነት ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል። በሥርዓተ ቅዳሴው ላይ ለተሳተፉት ሁሉ የየምስራች መግለጫ የትንሳኤ እንቁላሎች በስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
ብፁዕነታቸው ከአምባሳደር ኩራኮቭ ጋር በመገናኘት የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በሴኔጋል ስላላት እንቅስቃሴና መገኘትም ተወያይተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X