ሰባት የአፍሪካ ሀገራት እስከ ጎርጎሮሳውያኑ 2027 በዓመት ከ6% በላይ እድገት እንደሚያስመዘግቡ የዓለም ባንክ ትንበያ አሳየ

ሰባት የአፍሪካ ሀገራት እስከ ጎርጎሮሳውያኑ 2027
ሰባት የአፍሪካ ሀገራት እስከ ጎርጎሮሳውያኑ 2027 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.04.2026
ሰብስክራይብ
ሰባት የአፍሪካ ሀገራት እስከ ጎርጎሮሳውያኑ 2027 በዓመት ከ6% በላይ እድገት እንደሚያስመዘግቡ የዓለም ባንክ ትንበያ አሳየ

​የዓለም ባንክ የቅርብ ጊዜው "የአፍሪካ ፐልስ" ሪፖርት፣ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት እ.ኤ.አ. በ2026 እና በ2028 መካከል ጠንካራ ዓመታዊ እድገት ያስመዘግባሉ የሚል ትንበያ አስቀምጧል።

​ቅደም ተከተል በጎርጎሮሳዊያኑ 2026 ፣ 2027 እና 2028​ከፍተኛ እድገት ያስመዘግባሉ ተብለው የሚጠበቁት የሚከተሉት ያካትታሉ፦

ጊኒ - 8.8% (2026)፣ 11.6& (2027) እና 10.7% (2028) በማስመዝገብ ትመራለች። ለዚህም ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርገው ግዙፉ የሲማንዱ የብረት ማዕድን ፕሮጀክት ሲሆን፣ እ.ኤ.አ እስከ 2030 የሀገሪቱን አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርትን በ26 በመቶ ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ - 8.0%፣ 6.9% እና 8.4% እድገት እንደምታስመዘግብ የተተነበየላት ሲሆን፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ አቅርቦትን እና የኢንዱስትሪ ግብዓትን በማሻሻል ለዚህ እድገት ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል።

ኡጋንዳ - 6.8%፣ 8.5% እና 8.1% ኢኮኖሚዋ ያድጋል የተባለ ሲሆን ከነዳጅ ምርት እና በኬንያ በኩል ከሚዘረጋው አዲስ የወጪ ንግድ የድፍድፍ ነዳጅ ማስተላለፊያ ተጠቃሚ ትሆናለች።

ሩዋንዳ - 7.2 በመቶ፣ 7.6 በመቶ እና፣ 7.3 በመቶ እንዲሁም ታንዛኒያ - 6.1ዐ በመቶ፣ 6.4 በመቶ እና 6.5 በመቶ እያስመዘገበች ሲሆን በግብርና፣ በአገልግሎት ዘርፍ እና በኢንዱስትሪ ሽግግር ላይ ያላቸውን ጠንካራ አፈጻጸም ይቀጥላሉ።

ቤኒን - 7.0%፣ 7.2% እና 7.3% ታስመዘግባለች ተብሎ የተተነበየ ሲሆን ከመዋቅራዊ ለውጦች እና ከግሎ-ጂግቤ የኢንዱስትሪ ቀጠና ተጠቃሚ ትሆናለች።

ኒጀር - 6.7%፣ 6.4% እና 6.1% እድገቷ በነዳጅ ምርት (በቀን ከ110 ሺህ በርሜል በላይ) የሚመራ ቢሆንም፣ እድገቱ ከቤኒን ጋር ያለውን የመጓጓዣ ውጥረት በመፍታት ላይ የተመሰረተ ይሆናል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0