የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ደህንነት ምክር ቤት የኢትዮጵያ የሰው ሠራሽ አስተውሎት አቅም በክልላዊ ደረጃ እንዲስፋፋ ጥሪ አቀረበ

የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ደህንነት ምክር ቤት
የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ደህንነት ምክር ቤት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.04.2026
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ደህንነት ምክር ቤት የኢትዮጵያ የሰው ሠራሽ አስተውሎት አቅም በክልላዊ ደረጃ እንዲስፋፋ ጥሪ አቀረበ

የምክር ቤቱ አባላት እና የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች በኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሥራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ ጉብኝቱ በሰው ሠራሽ አስተውሎት እና በተግባራዊ ሥራዎቹ ላይ ያተኮረ የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብር አካል ነበር ሲል ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።

​በአፍሪካ ሕብረት እና በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ፣ ጉብኝቱ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያስመዘገበችውን ውጤት ለማሳየትና ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የዕውቀት ሽግግር ለማድረግ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።

አምባሳደሮቹ ጉብኝቱን በማስመልከት በሰጡት አስተያየት፥ የኢትዮጵያ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አቅም ወደ ሌሎች የቀጣናው ሀገራት ሊስፋፋ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0