ሕዳሴን ጨምሮ በተለያዩ ግድቦች ግንባታ ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች በአንድ ተቋም ሥር ለማሰባሰብ መታቀዱ ተገለፀ
11:26 20.04.2026 (የተሻሻለ: 12:29 20.04.2026)
© Sputnik
ሰብስክራይብ
ሕዳሴን ጨምሮ በተለያዩ ግድቦች ግንባታ ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች በአንድ ተቋም ሥር ለማሰባሰብ መታቀዱ ተገለፀ
ውጥኑ፣ ከሚያዚያ 9 እስከ ሚያዚያ 12 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ የመሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ሳምንት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡
እቅዱ፣ በአንድ ተቋም ሥር የሚሰባሰቡት ባለሙያዎች፣ ከሀገር አቀፍ አልፎ ዓለም አቀፍ ኮንትራክተር እንዲሆኑ ለማድረግ ሐሳብ እንዳለው በመድረኩ ተገኝተው ሃሳባቸውን ያስረዱት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ገልጸዋል፡፡
ይህም እቅድ ወደ ተግባር እስኪቀየር ድጋፍ እንደሚሰጥ መናገራቸውን የሀገር ውስጥ የገል ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ተቋማዊ አስተዳዳር ባለመኖሩ ምክንያት ለግድቡ ሥራ ዋንኛው ፈታኝ ችግር እንደነበረና ከካሣ ክፍያ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ 450 ሚሊዮን ዶላር ኪሣራ እንዳጋጠማት በተሞክሮነት ጠቅሰዋል ተብሏል።
ቪዲዮ፦ የሕዳሴ እና የኮይሻ ግድቦች የግንባታ እንቅስቃሴ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X