ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ኤም23 በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት፣ የተኩስ አቁም ክትትል እና በእስረኞች መለቀቅ ላይ ተስማሙ - የጋራ መግለጫ
16:09 19.04.2026 (የተሻሻለ: 17:32 19.04.2026)

ሰብስክራይብ
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ኤም23 በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት፣ የተኩስ አቁም ክትትል እና በእስረኞች መለቀቅ ላይ ተስማሙ - የጋራ መግለጫ
"የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት እና ኤም23 ታጣቂ ቡድን በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለሚገኙ ወገኖች ሕይወት አድራሽ ሰብአዊ ድጋፍ ማቅረብ ወሳኝ መሆኑን የተስማሙ ሲሆን፤ የሰብአዊ ተደራሽነት እና የፍትህ ጥበቃ ፕሮቶኮልን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ መሻሻል አሳይተዋል" ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በሁለቱ ወገኖቹ መካከል የተደረሱ ዋና ዋና ስምምነቶች፦
🟠 ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕግ መገዛት፦ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ሕግን እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ሕገ-መንግሥት መሠረታዊ መርሆችን ጨምሮ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕጎችን ማክበር ያካትታል፡፡
🟠 በሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ከመፈጸም መቆጠብ፦ የምግብ አቅርቦቶችን፣ ሰብሎችን፣ ከብቶችን፣ የውኃ ሥርዓቶችን፣ የመስኖ መሠረተ ልማቶችን፣ ቴሌኮሙኒኬሽንን፣ ኢነርጂን፣ ሆስፒታሎችን እና ትምህርት ቤቶችን እና ሌሎችም፡፡
🟠 የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ አካላትን ማክበር እና መጠበቅ፦ የአካባቢው ድንገተኛ ምላሽ ሰጪዎችን እና እርዳታ ተቀባዮችን መጠበቅ እንዲሁም በሰላም እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ፡፡
🟠 የእርዳታ ቁሳቁሶችን አቅጣጫ ከማስለወጥ እና ከመዘረፍ መቆጠብ
🟠 ለሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች፣ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ነፃ እንቅስቃሴን ጨምሮ ፈጣን፣ ያልተገደበ እና አስተማማኝ የሰብአዊ ተደራሽነትን ማመቻቸት፤
🟠 የተኩስ አቁም የክትትል ዘዴን ወደ ሥራ ማስገባት ሲሆን፤ የመጀመሪያው የማረጋገጫ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተባበሩት መንግሥታት የመረጋጋት ተልዕኮ ድጋፍ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንዲጀምር ማድረግ፤
🟠 ባለፈው መስከረም 4, 2018 ዓ.ም የተፈረመውን የታሰሩ ሰዎችን የመልቀቂያ ሥርዓት መሠረት በማድረግ በአሥር ቀናት ውስጥ እስረኞችን መልቀቅ።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X