በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለሚሰማሩ የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎች አምራቾች ለ4 ዓመት ከሊዝ ክፍያ ነጻ ይደረጋሉ – ኮርፖሬሽኑ
14:26 19.04.2026 (የተሻሻለ: 14:34 19.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለሚሰማሩ የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎች አምራቾች ለ4 ዓመት ከሊዝ ክፍያ ነጻ ይደረጋሉ – ኮርፖሬሽኑ
የኢትዮጵያ የ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣ በኢኮኖሚ ዞኑ ውስጥ በዘርፉ ለሚሰማሩ ድርጅቶች የማምረቻ ቦታ በሊዝ እንዲወስዱ”በዓይነቱ ልዩ የሆነ” ያለውን ጥሪ አቅርቧል፡፡
ጥሪውን የሚቀበሉ አልሚዎች፦
በዘርፉ ከአንድ ዓመት በላይ ልምድ እንዲኖራቸው፣
የማምረቻ ሼዱን በራሳቸው ወጪ መገንባት የሚችሉ እና
ለአገር ውስጥ ግብዓቶች ቅድሚያ በመስጠት ጠንካራ የገበያ ትስስር የመፍጠር ፍላጎት እንዲኖራቸው ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም የሥራ ዕድል በመፍጠር እንዲሁም የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማምጣት ረገድ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉ መሆን እንደሚኖርባቸው ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X