ግብፃዊው አልሚ በካይሮ አቅራቢያ የሚገነባ የ27 ቢሊዮን ዶላር አዲስ ከተማ እቅድ ይፋ አደረገ - መገናኛ ብዙኃን

ግብፃዊው አልሚ በካይሮ አቅራቢያ የሚገነባ የ27 ቢሊዮን ዶላር አዲስ ከተማ እቅድ ይፋ አደረገ - መገናኛ ብዙኃን
ግብፃዊው አልሚ በካይሮ አቅራቢያ የሚገነባ የ27 ቢሊዮን ዶላር አዲስ ከተማ እቅድ ይፋ አደረገ - መገናኛ ብዙኃን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.04.2026
ሰብስክራይብ
ግብፃዊው አልሚ በካይሮ አቅራቢያ የሚገነባ የ27 ቢሊዮን ዶላር አዲስ ከተማ እቅድ ይፋ አደረገ - መገናኛ ብዙኃን

​ ከ2 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ በሆነ ቦታ ላይ የሚንጣለለው እና "ዘ ስፓይን" የተሰኘው ይህ ፕሮጀክት፤ በታላት ሙስጠፋ ግሩፕ የሚገነባ ሲሆን፣ 165 የመኖሪያ፣ የንግድ እና የቢዝነስ ሕንፃዎችን ያካትታል ሲሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

​ ፕሮጀክቱ ከ155 ሺህ በላይ የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጥር እና በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጎብኚዎችን እንደሚስብ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሂሻም ታላት ሙስጠፋ መናገራቸው ተጠቅሷል።
​

ሙስጠፋ፣ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ዘ ስፓይን አሁን እየተገነባ ላለው ዘመናዊ ኢኮኖሚ እንደ የጀርባ አጥንት ነው” ብለዋል።

​አክለውም፣ ኢንቨስትመንቱ ከግብፅ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት 1 በመቶ ያህል እንደሚሸፍን እና ወደፊትም ለመንግሥት በግምት 15.78 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የታክስ ገቢ ያስገኝል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

​በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0