“ጠፈር ሩቅ አይደለም” - ኢትዮጵያዊት ዕጩ ጠፈርተኛ እመቤት ሙሀባው

ሰብስክራይብ

“ጠፈር ሩቅ አይደለም” - ኢትዮጵያዊት ዕጩ ጠፈርተኛ እመቤት ሙሀባው

‍ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ዕጩ ጠፈርተኛ እመቤት ሙሀባው የጠፈር ምርምር ዘርፍ ለኢትዮጵያውያን ዝግ እንዳልሆነና ወጣቶች በዘርፉ ለመሰማራት ድፍረት ሊኖራቸው እንደሚገባ ገለጸች።

የየጠፈር ትውልድ አማካሪ ምክር ቤት ( Space Generation Advisory Council) የአፍሪካ ቀጣና አስተባባሪ የሆነችው እመቤት በኤ. ኤል.ኤክስ (ALX) ኢትዮጵያ እና በኢዲዛ (Ideeza) የፈጠራ ስቱዲዮ ትብብር በተዘጋጀ የዩሪ ጋጋሪን መታሰቢያ (ዩሪ ናይት) መርሃ ግብር ላይ ተገኝታ ልምድና ተሞክሮዋን አካፍላለች፡፡

እመቤት በህዋ ምርምርና ምህንድስና ዘርፍ የኢትዮጵያውያን ተሳትፎ ሊያድግ እንደሚገባ አሳስባለች።

ወጣቶች በራሳቸው እንዲተማመኑና ተሰጥዖቸውን ከፍላጎታቸው ጋር እንዲያጣጥሙ የመከረችው እመቤት፣ የኤሮስፔስ ኢንጂነር የመሆን ህልም ያላቸውን ለማገዝና ለማማከር ቃል መግባቷን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

እመቤት እ.ኤ.አ በ2029 የጠፈር በረራ የምታደርግ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ዕጩ ጠፈርተኛ ነች።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0