በግብፅ ብርቅዬ የግሪክ እና የሮማውያን ዘመን ቅርሶች ተገኙ - የሀገሪቱ የቱሪዝም ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

በግብፅ ብርቅዬ የግሪክ እና የሮማውያን ዘመን ቅርሶች ተገኙ - የሀገሪቱ የቱሪዝም ሚኒስቴር

ግኝቱ በምንያ ግዛት በቅርቡ ለተመዘገቡት ተከታታይ ታላላቅ የአርኪኦሎጂ ግኝቶች ተጨማሪ መሆኑንና የግብፅን ስልጣኔ ብልጽግና እና ብዝሃነት የሚያጎላ መሆኑን የቱሪዝም እና የጥንታዊ ቅርሶች ሚኒስትር ሸሪፍ ፋቲ ገልጸዋል።

​ቅርሶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

▶አንዳንድ በጥበብ በተሰሩ ጨርቃጨርቆች እንደተጠቀለሉ ያሉ ሙሚዎች (በሬሳ ማድረቂያ የቆዩ በድኖች)፤ 

▶ ደመቅ ያሉ ቀለማት ያሏቸው ከእንጨት የተሰሩ ሬሳ ሳጥኖች፤

▶በአፍ ውስጥ ወይም አጠገብ የተቀመጡ ሦስት የወርቅ እና አንድ የነሐስ ምላሶች፤

▶የተቃጠሉ ቅሪቶች እና የእንስሳት አጥንቶች ያሉባቸው ማሰሮዎች የያዙ ከኖራ ድንጋይ የተሰሩ የመቃብር ክፍሎች፤

▶ ከሸክላ እና ከነሐስ የተሰሩ ምስሎች፣ ሀርፖክራተስን እና ትንሽ የኩፒድ ሃውልትን ያካትታሉ።

​ ግኝቱ በግሪክ እና በሮማውያን ዘመን በአል-በሃንሳ ከተማ የነበሩ የቀብር ሥነ-ሥርዓቶችን በተመለከተ አዲስ እውቀት የሚሰጥ መሆኑን የጥንታዊ ቅርሶች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ሂሻም ሊቲ ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0