በአማራ ክልል በዘጠኝ ወራት ከቱሪዝም 12 ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል - የቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ

ሰብስክራይብ

በአማራ ክልል በዘጠኝ ወራት ከቱሪዝም 12 ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል - የቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ

በክልሉ የሚገኙ ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊና ሃይማኖታዊ የቱሪስት መዳረሻዎችን 15 ሚሊዮን 995 ሺህ በላይ በሚሆኑ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች መጎብኘታቸውን ተጠቁሟል። 

ከእነዚህም ውስጥ 40 በመቶ የሚሆኑት ተጓዦች ለዘመድ ጥየቃ ወደ ክልሉ ያቀኑ ሲሆን፣ 37 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ለዕረፍትና ለመዝናናት የመጡ ቱሪስቶች ናቸው። ቀሪዎቹ ጎብኝዎች ለተለያዩ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ለሥራ ጉዞ ማድረጋቸውን ቢሮ አክሎ አስታውቋል።

በቀጣይም የቱሪስት መዳረሻዎችን መሠረተ ልማት በማሟላትና አገልግሎቶችን በማዘመን የጎብኝዎችን ቆይታ ይበልጥ በማራዘም ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ መታቀዱን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ቪዲዮ፡- ጎንደር ከተማ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0