ሩሲያ እና ቻይና የአንድ ወገን ጥገኝነት የለባቸውም ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

ሩሲያ እና ቻይና የአንድ ወገን ጥገኝነት የለባቸውም ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

​ የሁለቱ ሀገራት የንግድ እና የኢነርጂ ትስስር ሚዛናዊ እና የጋራ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ መሆኑን ሰርጌ ላቭሮቭ በአንታሊያ ዲፕሎማሲያዊ ፎረም ላይ ገልጸዋል።

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

የኒዮ-ናዚ (የናዚአዊነት ጽንፈኝነት) አስተሳሰብ በጀርመን እና በፊንላንድ በግልጽ እያቆጠቆጠ ነው፤ እንግሊዝ ለረጅም ጊዜ ለእንደዚህ አይነት ሀሳቦች ቅርብ ሆና ቆይታለች፡፡

በኢራን የነበረው የአሜሪካ ዘመቻ አንዱ ግብ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፈውን የነዳጅ ፍሰት መቆጣጠር ነበር፡፡

ኔቶ አስቸጋሪ ምዕራፍ ውስጥ እያለፈ ነው፤ ነገር ግን ሩሲያ በውስጥ ጉዳዩ ጣልቃ አትገባም፡፡

ዩክሬንን የሚያካትት አዲስ ወታደራዊ ግንባር ለመፍጠር አውሮፓ ውስጥ እቅድ እየተዘዋወረ ነው፤ ይህም አሁንም ቢሆን "ጠብ ፍለጋ" ይሆናል ብለዋል፡፡

ሩሲያ ከአሜሪካ አስተዳደር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች እና ማዕቀቦች ላይ በርካታ አለመግባባቶች እንዳሉ ትገነዘባለች፤ ዋሽንግተን ከሞስኮ ጋር ያላትን የወደፊት የኢኮኖሚ ግንኙነት እንዴት እንደምታየውም እውነተኛ ውይይት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0