በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ የሚገኝ የዝሆን መንጋ የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠበት ተገለፀ
14:10 18.04.2026 (የተሻሻለ: 15:41 18.04.2026)
ሰብስክራይብ
🇪🇹 በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ የሚገኝ የዝሆን መንጋ የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠበት ተገለፀ
— Sputnik Ethiopia (@sputnik_ethio) April 18, 2026
🐘 በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ የዝሆኖች ቁጥር ከ13 ዓመታት በፊት 1,000 ከነበረበት አሁን ላይ ወደ 215 ዝቅ ማለቱን የመጠለያው ተወካይ ጠቅሶ የውጭ ሚዲያ… pic.twitter.com/7szmeYBtjv
በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ የሚገኝ የዝሆን መንጋ የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠበት ተገለፀ
በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ የዝሆኖች ቁጥር ከ13 ዓመታት በፊት 1,000 ከነበረበት አሁን ላይ ወደ 215 ዝቅ ማለቱን የመጠለያው ተወካይ ጠቅሶ የውጭ ሚዲያ ዘግቧል።
ሕገ-ወጥ አደን፣ በመጠለያው ውስጥ የሚመሰረቱ አዳዲስ ሰፈራዎች፣ የደህንነት ችግሮች፣ የደን መጨፍጨፍ፣ የማዕድን ቁፋሮ እና የግጦሽ መሬት ለዝሆኖቹ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ እንደ ዋና ምክንያቶች ተጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ኃላፊን የጠቀሰው ዘገባው፣ ሕገ-ወጥ አደንን እና የዱር እንስሳት ዝውውርን ለመቆጣጠር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጽፏል።
እ.ኤ.አ. በ1978 የተመሠረተው የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ 6,982 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት የሚሸፍን ሲሆን፣ የ231 የአእዋፍ እና የ31 አጥቢ እንስሳት ዝርያዎች መገኛም መሆኑን መተገልጿ።
ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ቪዲዮ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X