እስራኤል ከሊባኖስ ጋር የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ታከብራለች?
እስራኤል እ.ኤ.አ. በ2024 የተደረገውን የቀድሞ ስምምነት እንዳደረገችው ሁሉ፣ አሁኑኑንም የተኩስ አቁም ስምምነት ለራሷ በሚያመች መልኩ ልትተረጉመው ወይም እንደገና ልታብራራው ትችላለች ሲሉ የሊባኖስ የፖለቲካ ተንታኝ ጆሴፍ ሄሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
እንደ ባለሙያው ገለጻ፣ ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው የተኩስ አቁም ስምምነት "በቅርጹ አዲስ አይደለም፤ ምክንያቱም ብዙዎቹ አንቀጾች በአሜሪካ አሸማጋይነት እ.ኤ.አ. ህዳር 27 2024 በተደረገው ስምምነት ላይ በሆነ መልኩ ተጠቅሰዋል" ይሁን እንጂ የቀድሞ ስምምነት በእስራኤል በኩል 15 ሺህ ጊዜ መጣሱን ሄሉ አስታውሰዋል።
የአሁኑን የተኩስ አቁም በተመለከተ፣ እስራኤል ከሊባኖስ ጋር "በታቀዱ ውይይቶች አመክንዮ ለመመራት ፍቃደኛ የሆነች ትመስላለች" ሲሉ ባለሙያው ገልጸዋል።
"በሊባኖስ እና በእስራኤል መካከል ያለውን ግዙፍ አለመግባባት ለመፍታት የሚያስችል እውነተኛ ሂደት እንደገና ካልተጀመረ በስተቀር፣ ግጭቱ 100 በመቶ አብቅቷል ማለት አንችልም" በማለት ሄሉ ደምድመዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X