የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር ለቀጣናዊ የትራንስፖርት ኮሪደሮች ፈጣን የፋይናንስ አቅርቦት እንዲመቻች ጥሪ አቀረቡ

ለቀጣናዊ የትራንስፖርት ኮሪደሮች ፈጣን የፋይናንስ አቅርቦት እንዲመቻች ጥሪ አቀረቡ
ለቀጣናዊ የትራንስፖርት ኮሪደሮች ፈጣን የፋይናንስ አቅርቦት እንዲመቻች ጥሪ አቀረቡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.04.2026
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር ለቀጣናዊ የትራንስፖርት ኮሪደሮች ፈጣን የፋይናንስ አቅርቦት እንዲመቻች ጥሪ አቀረቡ


ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ፣ "ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ላላትና የውጭ ንግዷ ሙሉ በሙሉ በቀጣናዊ ትስስር ላይ ለመሠረተች ሀገር፣ ቀልጣፋ የመንገድ ኮሪደሮች አማራጭ ሳይሆኑ የኅልውና ጉዳይ ናቸው" ሲሉ በ28ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተናግረዋል፡፡


በኢኮኖሚ ኮሪደሮች ላይ ፈጣን ኢንቨስትመንት ለማካሄድ፣ የንግድ እንቅስቃሴን ለማሳለጥ፣ የውድድር አቅምን ለማሳደግ እና በቀጠናው የሥራ እድል ለመፍጠር የትራንስፖርት ኮሪደር ልማቱ ቁልፍ መሆኑንም ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ስብሰባው ከ9,100 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍኑ አራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ኮሪደሮች አፈጻጸም የገመገመ ሲሆን፣ ለእነዚህም 3.8 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስትመንት መታቀዱን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0