ኢትዮጵያ በ2026 ከአፍሪካ ቀዳሚውን የኢኮኖሚ ዕድገት እንደምታስመዘግብ አይ ኤም ኤፍ ተነበየ
19:23 17.04.2026 (የተሻሻለ: 19:26 17.04.2026)

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በ2026 ከአፍሪካ ቀዳሚውን የኢኮኖሚ ዕድገት እንደምታስመዘግብ አይ ኤም ኤፍ ተነበየ
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በፈረንጆቹ 2026 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ9.2 በመቶ በማደግ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዝ ቅድመ ትንበያውን አስቀምጧል።
የኢትዮጵያ ዕድገት በአፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ አላቸው ከሚባሉት ኡጋንዳ (7.5 %)፣ ሩዋንዳ (7.2 %)፣ ኬንያ (4.5%)፣ ናይጄሪያ (4.1%) እና ደቡብ አፍሪክ (1.0%) እንደሚበልጥ ተገልጿል።
የመንግሥት የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች ለአዎንታዊ ትንበያው ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጋቸው ተጠቁሟል።
ሆኖም የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ የነዳጅ እና ማዳበሪያ ዋጋን ከፍ በማድረግ በገቢ ንግድ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል አበዳሪ ድርጅቱ አመልክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X