የናይጄሪያ የደህንነት ተቋማት በሽብር ጥቃት ስጋት በአየር ማረፊያዎች እና እስር ቤቶች አካባቢ ጥበቃ አጠናከሩ

ናይጄሪያ
ናይጄሪያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.04.2026
ሰብስክራይብ
የናይጄሪያ የደህንነት ተቋማት በሽብር ጥቃት ስጋት በአየር ማረፊያዎች እና እስር ቤቶች አካባቢ ጥበቃ አጠናከሩ

የናይጄሪያ ፖሊስ ኃይል፣ የኢሚግሬሽን አገልግሎት እና የማረሚያ አገልግሎት በተለያዩ ተቋማት የደህንነት ጥበቃ ማጠናከራቸውን የአካባቢው የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

አሸባሪ ቡድኖች በንናምዲ አዚኪዌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ በኩጄ የማቆያ ማዕከል እና በኒጀር ግዛት በሚገኝ አንድ ማረሚያ ቤት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር አቅደው እንደነበር መገናኛ ብዙኃኑ ጠቅሰዋል።


የአየር ማረፊያ ፖሊስ ዕዝ ቃል አቀባይ አዴኦላ ሙሀመድ “በደህንነት ተቋማት መካከል ውጤታማ የመረጃ ልውውጥ እና ትብብር በመኖሩ ዕዙ ከየትኛውም ስጋት አንድ እርምጃ ቀድሞ ይገኛል” ብለዋል።


ዕዙ ሊከሰቱ የሚችሉ የትኛውም ዓይነት የደህንነት ስጋቶችን ነቅቶ እንደሚጠብቅም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።


የናይጄሪያ ኢሚግሬሽን አገልግሎት ቃል አቀባይ አኪንሶላ አኪንላቢ በበኩላቸው “ፖሊስ እና የጦር ኃይሉ ይህንን ስጋት እየተቆጣጠሩት እንደሆነ እርግጠኞች ነን” ሲሉ ገልጸዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0