የሰው ልጅ መገኛ የሆነችው አፋር በድንቅነሽ (ሉሲ) የተሰየመ ሙዚየም ልትገነባ ነው
15:53 17.04.2026 (የተሻሻለ: 16:03 17.04.2026)

ሰብስክራይብ
የሰው ልጅ መገኛ የሆነችው አፋር በድንቅነሽ (ሉሲ) የተሰየመ ሙዚየም ልትገነባ ነው
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን እና የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ሙዚየሙን በአፋር ክልል መዲና ሰመራ ለመገንባት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ቤተ-መዘክሩ ከ329.8 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባ ሲሆን በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ተገልጿል።
የቅርስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው፤ ሙዚየሙ የቱሪስት ፍሰትን ከመጨመር ባለፈ የሰው ልጅ አመጣጥን እና የአፋርን ባሕል ለዓለም ለማስተዋወቅ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።
ሙዚየሙ ለዘርፉ ተመራማሪዎች ምቹ ሁኔታ ይፈጥራልም ተብሏል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X