- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

የዓለም አሃዳዊ ዋልታ የኃይል ስርዓት እያከተመ ነው ?

የዓለም አሃዳዊ ዋልታ የኃይል ስርዓት እያከተመ ነው ?
ሰብስክራይብ

''ዋሽንግተን መሪዎችን በመግደል እና ኃይሏን በመጠቀም ኢራንን በአጭር ግዜ ውስጥ አንበረክካለሁ ብላ አስባ ነበር። በተቃራኒው ኢራን ድብደባዎቹን ተቋቁማ፤ መከላከሏን ቀጠለች እንዲሁም የጦር ሜዳውን ወደ ባሕረ ሰላጤው፣ ወደ አረቦች እና ወደ ሌሎች የዓለም ክፍሎች አስፋፍታለች። በዚህም አሜሪካ የበላይነቷን አሳያለሁ ብላ ድክመቷን አጋልጣለች ”- በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሶሺዮ አንትሮፖሎጂ መምህር መሃመድ አወል ሀጎስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው ሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በክፍል አንድ የዓለም አሃዳዊ ዋልታ የኃይል ስርዓት እያከተመ ስለመሆኑ ከጂዮፖለቲካዊ አኳያ ከወራቤ ዩኒቨርስቲ መምህር መሃመድ አወል ሀጎስ ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛው ክፍል በአፍሪካ ያለውን የጸጥታ እና የውጭ ኃይሎች ጣልቃገብነት ጉዳይ ከዶ/ር ሙከረም ሚፍታህ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናቶች ረዳት ፕሮፌሰር ጋር ቃኝተነዋል።
በመጨረሻው ክፍል ከሚያዝያ 8- 2026 ፣ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአደጋ ስጋት አስተዳደር አቅምን በተመለከተ ከቻርሎት ኖርማን፣ የጋና ብሔራዊ የአደጋ አስተዳደር ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ መላመድ እና የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዳይሬክተር ጋር ዳሰነዋል።
ሙሉውን መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0