የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ በኢትዮጵያ የቤተሰብ ገቢ ላይ እስከ 4.3 በመቶ ቅናሽ ሊያስከትል እንደሚችል ተነገረ

ሰብስክራይብ

የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ በኢትዮጵያ የቤተሰብ ገቢ ላይ እስከ 4.3 በመቶ ቅናሽ ሊያስከትል እንደሚችል ተነገረ

የግጭቱ መራዘም በምግብ እና በትራንስፖርት ዋጋ ላይ በሚፈጥረው ጫና ምክንያት፤ የኢትዮጵያውያን አማካይ የቤተሰብ ገቢ ከ1.5 እስከ 4.3 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ዓለም ባንክ ባወጣው አዲስ ሪፖርት አስጠንቅቋል።

የኢትዮጵያ ቤተሰቦች ከጠቅላላ ወጪያቸው 58.5 በመቶውን ለምግብ የሚያውሉ በመሆናቸው ለዋጋ ግሽበት ተጋላጭ እንደሚሆኑም ተጠቁሟል።

62 በመቶ የሚሆኑት የከተማ ቤተሰቦች የሕዝብ ትራንስፖርት ተጠቃሚ በመሆናቸው በነዳጅ ምክንያት የሚመጣ የዋጋ ጭማሪ ገቢያቸውን በእጅጉ ይጎዳዋል መባሉን ጠቅሶ የዘገበው የሀገር ውስጥ ሚዲያ ነው።

ከባህረ ሰላጤ ሀገራት የሚላከው የውጭ ምንዛሬ (ከ6 ቢሊዮን ዶላር በላይ) በቀውሱ ምክንያት ከቀነሰ የዜጎችን የመግዛት አቅም የበለጠ እንደሚያዳክምም ተገልጿል።

የዓለም ባንክ የችግሩን ጫና ለመቀነስ መንግሥት የፖሊሲ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ ምክረ-ሐሳብ አቅርቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0