ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የጂኦፓርክ መዝገብ የመጀመሪያዋን ሥፍራ ለማስመዝገብ ለዩኔስኮ የጥናት ሰነድ አቀረበች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የጂኦፓርክ መዝገብ የመጀመሪያዋን ሥፍራ ለማስመዝገብ ለዩኔስኮ የጥናት ሰነድ አቀረበች

በቀረበው የጥናት ሰነድ ውስጥ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይ እና አማራ ክልሎች የሚገኙ ጂኦፓርኮች በእጩነት መለየታቸውን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ፤ ጥናቱ ከዩኔስኮ እና ከኮሪያ የጂኦፓርክ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የተከናወነ መሆኑን በመጥቀስ፤ ቢያንስ አንዱን ስፍራ በዓለም አቀፍ መዝገብ ላይ ለማስፈር ግብ መቀመጡን ተናግረዋል።

ምዝገባው የሀገሪቱን የቱሪስት መዳረሻዎች ለማስፋፋት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግ እና ዘላቂ የቱሪዝም ልማትን ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና እንደሚኖረውም ተጠቁሟል።

ይህ ተነሳሽነት ኢትዮጵያ ከባሕላዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች በተጨማሪ ያሏትን የተፈጥሮ የጂኦሎጂ ሀብቶች ለዓለም ለማስተዋወቅ አዲስ ዕድል ይፈጥርላታል ማለታቻውን የዘገበው የሀገር ውስጥ ሚዲያ ነው።

ተንቀስቃሽ ምሥሉ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘውን የሌጲስ ኢኮቱሪዝም መንደር ያሳያል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0