በማዳጋስካር ፕሬዚዳንት ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ

የማዳጋስካር ፕሬዚዳንት
የማዳጋስካር ፕሬዚዳንት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.04.2026
ሰብስክራይብ
በማዳጋስካር ፕሬዚዳንት ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ

የማዳጋስካር ፕሬዚዳንት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ሃሪ ሎረንት ራሃድዛሶን፤ የግድያ ሙከራው በፕሬዚዳንቱ ሚካኤል ራንድሪያኒሪና እና በባለቤታቸው ላይ እንደተደረገ መግለጻቸውን አንድ የሀገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል።

አምስት ድሮኖች ከፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ቤት በላይ ሌሊቱን እንደበረሩ ነው የኮሚኒኬሽን ኃላፊው የገለጹት። የፕሬዚዳንቱ የደህንነት አገልግሎት በጣልቃ ገብነት የድሮን ቁጥጥርን የማጨናገፍ አቅም ያላቸው ፀረ-ድሮን ስርዓቶች በመታጠቃቸው ሰው አልባ ተሽከርካሪዎቹ አልፈው መሄዳቸውን አክለዋል።

ራሃድዛሶን በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ መጀመሩን አስታውቀዋል። ድሮኖቹ ጥይት የመሸከም አቅም እንዴላቸው የገለጹት ኃላፊው፤ ነገር ግን የመኖሪያ ቤቱን እንቅስቃሴዎች እና በተለያዩ ክፍሎች ውስጥ ያሉ ሰዎችን ብዛት ለመከታተል የኢንፍራሬድ የክትትል መሳሪያዎች የተገጠሙላቸው ናቸው ብለዋል።

የፕሬዚዳንቱ ተወካይ፤ ሙከራው የማላጋሲ አመራር የሀገሪቱን የነዳጅ አቅርቦት ምንጮች ለማስፋት ባለው ፍላጎት ያልተደሰቱ "የውጭ ኃይሎች የማስፈራራት ሙከራ" ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል። በተጨማሪም የሪፐብሊኩ የስለላ አገልግሎት ቅዳሜ ሚያዚያ 10 የተወሰኑ ኃይሎች የሀገሪቱን ፓርላማ ሕንፃ የማቃጠል ዕቅድ እንዳላቸው መረጃ ደርሶታል ብለዋል።

የማላጋሲ ባለሥልጣናት በሚያዝያ ወር መጀመሪያ መፈንቅለ መንግሥት እና ፕሬዚዳንቱ ላይ የግድያ ሙከራ በማቀድ 13 ግለሰቦችን ከሰዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0