የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በማዳበሪያ ወጪ ንግድ ላይ የሚፈጥረው ገደብ የዓለም የምግብ ዋስትናን ስጋት ውስጥ እንደሚከት ፋኦ አስጠነቀቀ

ሰብስክራይብ

የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በማዳበሪያ ወጪ ንግድ ላይ የሚፈጥረው ገደብ የዓለም የምግብ ዋስትናን ስጋት ውስጥ እንደሚከት ፋኦ አስጠነቀቀ

የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ የማዳበሪያ ገበያን በማወኩ በወርሃ መጋቢት የዓለም የምግብ ዋጋ ለሁለተኛ ተከታታይ ወር ጭማሪ ማሳየቱን የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) ገልጿል።

ተቋሙ፤ ሀገራት በኃይል (ኢነርጂ) እና በማዳበሪያ ምርቶች ወጪ ንግድ ላይ ገደብ እንዳይጥሉ ያሳሰበ ሲሆን እንዲህ ያሉ እርምጃዎች ገበያውን ይበልጥ እንደሚያጠብቁት አስጠንቅቋል።

በአሜሪካ እና በኢራን ግጭት ምክንያት የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት ወሳኝ የሆነውን የንግድ መስመር ክፉኛ ጎድቶታል። እንደ የተባበሩት መንግሥታት የንግድ እና ልማት ጉባኤ መረጃ ከሆነ፤ ወደ ዓለም ገበያ ከሚላከው ማዳበሪያ ውስጥ ሲሶ የሚሆነው በዚህ መስመር የሚያልፍ ነው።

የአሁኑ ስጋት፤ የዩክሬን ግጭት በዓለም አቀፍ ደረጃ የምግብ እና የማዳበሪያ ዋጋ ንረት ካስከተለበት የ2022ቱ ክስተት የከፋ መሆኑን ፋኦ አስታውቋል።

የወቅቱ ቀውስ እ.ኤ.አ በ2026 መገባደጃ ላይ ይከሰታል ተብሎ ከሚጠበቀው ከባድ የኤል ኒኞ ድርቅ ጋር ከተገጣጠመ፤ "አደገኛ ማዕበል" ሊፈጠር እንደሚችል ድርጅቱ አክሎ ገልጿል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0