ቶጎ እና የመርኬተር ካርታ፦ የአፍሪካን ትክክለኛ መጠን በዓለም መድረክ ላይ ለማሳየት የሚደረግ ትግል

ሰብስክራይብ

ቶጎ እና የመርኬተር ካርታ፦ የአፍሪካን ትክክለኛ መጠን በዓለም መድረክ ላይ ለማሳየት የሚደረግ ትግል

ቶጎ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለዘመናት ሲያገለግል የቆየውን የመርኬተር ካርታ እንዲጣል ግፊት እያደረገች ሲሆን ይበልጥ ትክክለኛ የሆነ ካርታን ሥራ ላይ እንዲውል የሚያስችል ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ መዘጋጀቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮበርት ዱሴ ገልጸዋል። በመጪው መስከረም በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ሊከናወን እንደሚችልም ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ ለብሪታንያ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት ቃል "በዓለም ካርታ ላይ የምናየው የአፍሪካ አህጉር ስፋት...ጂኦግራፊያዊ እውነታውን የሚያንጸባርቅ አይደለም" ብለዋል።

ይህ ጉዳይ ለምን አስፈለገ? ዝርዝሩ እነሆ፦

የመርኬተር ካርታ ከእውነታው ጋር ያለው ልዩነት፦ በ1569 ለመርከብ ጉዞ እንዲያመች ተደርጎ የተዘጋጀው የመርኬተር ካርታ፤ የሀገራትን ትክክለኛ መጠን ያዛባል። የሰሜኑን የዓለም ክፍል አግዝፎ ሲያሳይ፤ አፍሪካን ግን አሳንሶ ያቀርባል። በእውነታው ግን አፍሪካ በካርታው ላይ ከምትታየው ግሪንላንድ በ14 እጥፍ ትበልጣለች።

የጂኦ-ፖለቲካዊ እና የአመለካከት ተፅዕኖ፦ እንደ የአፍሪካ ኅብረት ባለሥልጣናት እና የዘመቻው አራማጆች ገለጻ፤ የመርኬተር ካርታ መዛባት አውሮፓን ማዕከል ያደረገ አመለካከትን የሚያጠናክርና ስለ አሕጉሪቱ ትክክለኛ ስፋትና አስፈላጊነት የተሳሳተ ግንዛቤ የሚፈጥር ነው።

የቀረበው መፍትሔ - የ "እኩል መሬት" ካርታ፦ በ2018 የተሠራው የእኩል መሬት ካርታ፣ የአኅጉራትን ቅርፅ ሳይቀይር ትክክለኛ መጠናቸውን አንፃራዊ በሆነ መልኩ ያሳያል። ይህም ከመርኬተር ካርታ የተሻለ፣ ፍትሐዊ እና ለአጠቃቀም አመቺ አማራጭ ነው።

"ካርታውን አስተካክሉ" ዘመቻ፦ በአፍሪካ ኅብረት ድጋፍ የሚደረግለትና በቶጎ የሚመራው ይህ ዘመቻ፤ መንግሥታት፣ ትምህርት ቤቶች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ትክክለኛውን ካርታ እንዲጠቀሙና የትምህርት ሥርዓታቸውን እንዲያሻሽሉ ያሳስባል።

ቪዲዮው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዱሴ በ2025 በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ያደረጉትን ንግግር ያሳያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0