ኬንያ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ላይ እስከ 24 በመቶ ጭማሪ አደረገች

ኬንያ
ኬንያ  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.04.2026
ሰብስክራይብ
ኬንያ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ላይ እስከ 24 በመቶ ጭማሪ አደረገች

የአሜሪካ እና ኢራን ግጭት የነዳጅ ምርቶች ማስመጫ ዋጋን በ68.7 በመቶ እንዲያሻቅብ በማድረጉ፤ የቤንዚን የችርቻሮ ዋጋ በ16.1 በመቶ እንዲሁም የናፍጣ ዋጋ ደግሞ በ24.2 በመቶ እንዲጨምር መደረጉን የሀገሪቱ የኢነርጂ እና ነዳጅ ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታውቋል።

ከባሕረ ሰላጤው ሀገራት ነዳጅ በከፍተኛ ሁኔታ የምታስመጣው ኬንያ፤ አሁን ላይ አንድ ሊትር ቤንዚን በ206.97 የኬንያ ሺሊንግ (1.60 ዶላር) እንዲሁም አንድ ሊትር ናፍጣ በ206.84 ሺሊንግ እየሸጠች ትገኛለች።

የዋጋ ጭማሪው በተጠቃሚው ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመቀነስ፤ ባለሥልጣኑ የነዳጅ ምርቶች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከ16 በመቶ ወደ 13 በመቶ ዝቅ እንዲል አድርጓል። አዲሱ የዋጋ ተመን ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት በርካታ አሽከርካሪዎች ወደ ነዳጅ ማደያዎች በመሄድ ታንከሮቻቸውን ሲሞሉ መታየታቸው ተዘግቧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0